Accountant I (አካውንታንት I)

  • ETHIOPIAN RADIATION PROTECTION AUTHORITY
  • Addis Ababa
  • Federal Government
  • Deadline Feb 26, 2020
3,934 (ETB Salary) Full time Accounting and Finance

የስራው መደብ ዝርዝር

2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-

·         የተለያዩ የክፍያ ጥያቄዎችን በማረጋገጥ፣ የመ/ቤቱን የተከፋይ እና የተሰብሳቢ ሂሳቦች መረጃበ መሰብሰብና በማጠናቀር የክፍያና የገቢ ሥራው በወቅቱ እንዲቀላጠፍ ማድረግ፡፡

2.2. ከሥራ መደቡ የሚጠበቁ ውጤቶችና ተግባራት

ውጤት 1፡ የተለያዩ ጥቃቅን የክፍያ ማዘዣዎችን ማዘጋጀት፣

·  ጥቃቅን የአገልግሎት፣ ግዴታና ዕቃ ግዥ ቅድሚያ ክፍያዎችን በማዘጋጀት ክፍያ ተፈጽሞ የተሟላ የወጭ ማስረጃ መቅረቡን በማረጋገጥ ሂሳቡ እንዲወራረድ ያደርጋል፣ ክፍያ የተፈጸመበት ንሰነድ ለሰነድ ያዥ/ለሚመለከተው አካል/ ያስተላልፋል፣

·  ከገንዘብ ያዥ የክፍያ ሠነድ በመረከብና በማጣራት እንዲተካ ያደርጋል፣

·  የህትመት ሽያጭ ገቢ ከንብረት የወጪ ደረሰኝ ጋር በማመሳክር የተሰበሰበውን ገቢ በማጠቃለያ ደረሰኝ /ቅጽ/ በማስፈር ፈስስ ለተደረገው ማስረጃ የሳጥን ወጭ ማዘዣ ያዘጋጃል፣

·  በስራ ላይ ባለ ደንብና መመሪያ መሰረት እንዲሰራባቸው የተፈቀዱ ቼክ፣ የገቢና የወጭ ማዘዣ ሰነዶችን በማረጋገጥ ከንብረት ክፍል ይረከባል ስለአጠቃቀሙ አስፈላጊውን ክትትል ያደርጋል፤

ውጤት 2፡ የተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦች መረጃን ማሰባሰብና ማጠናቀር፤

·         ተሰብሳቢ፣ ተንጠልጣይ ሂሳቦችንና የተለያዩ ክፍያዎች ዝርዝር ያዘጋጃል፣

·         ተሰብሳቢ ሂሣቦችን ደረሰኝ በመቁረጥ በወቅቱ እንዲወራረድ ያደርጋል፣ በሌጀር ላይ ይመዘግባል፣ መረጃውንም ይይዛል፣

·         ተከፋይ የሆኑ ሂሳቦችን በማጣራት ለባለጥቅሙ እንዲከፈል የክፍያ ማዘዣ ያዘጋጃል፣ በሌጀር ላይ ይመዘግባል፣ መረጃውንም ይይዛል፣

·         ያልተወራረዱ ልዩ ልዩ ተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦችን በቆይታ ጊዜ ለይቶ በማጠናቀር እንዲወራረዱ ሪፖርት ያደርጋል፣

·         ከልዩ ልዩ ገቢዎች፣ ከወጪ ተመላሽ ፣የአደራ ሂሣቦች የገቢ ደረሰኝ ያዘጋጃል፣

·         የተመዘገቡትን የሂሣብ ሠነዶች በመለየት በቅደም ተከተል እንዲደራጅ ያደርጋል፣

III. የሥራው ባህሪ መግለጫዎች

3.1  የሥራ ውስብስብነት

·         ሥራው የክፍያ ሰነድ ማዘጋጀት፣ ለተሰብሳቢ ሂሣቦች ደረሰኝ ማዘጋጀት፣ ልዩ ልዩ መረጃዎችን ማጠናቀር፣ ያልተወራረዱ ልዩ ልዩ ተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦችን መከታተል የሚጠይቅ ሲሆን፣ ሥራው ሲከናወን የመንግስት ንየፋይናንስ አዋጅ፣ ደንብና መመሪያያ ልተከተለ የጥቃቅን ግዥና ክፍያ ጥያቄ ሊቀርብ ስለሚችልና የተከፋይ ሂሳቦች በወቅቱ ተጣርተው እንዲከፈሉ ባይደረግ በመ/ቤቱ በጀት ላይ ተጽኖ ያሳድራል፣ ይህን ችግር ለመፍታት መረጃዎችን በጥንቃቄ መርምሮ ማሳለፍ፣ መረጃዎችን ወደ ኋላ ተመልሶ ማጣራት ስህተቶችን በማረም ችግሩ የሚፈታ ይሆናል፡፡  

 

3.2  ራስን ችሎ መሥራት

3.2.1 ሥራው የሚከናወንበት አግባብ

 

·         ሥራው አዋጆች፣ ደንብና መመሪያዎችን በመከተል የሚከናወን ሲሆን ውሳኔ የሚሹ ጉዳዩች ከኃላፊ በሚሰጥ የአሰራር መመሪያ መሠረትይፈጸማል፣

 

3.2.2   ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ

·         ሥራው አዋጆች ደንብና መመሪያዎችን ተከትሎ ስለመሰራቱ እንዲሁም በተሰጠ መመሪያ መሠረት የጥራት ደረጃውን ጠብቆ ስለመከናወኑ በቅርብ ኃላፊው ክትትልና ድጋፍ ይደረግበታል፡፡

3.3 ተጠያቂነት

3.3.1 ተጠያቂነት ለሥራው ጤት /Responsibility for Impact/፣

·         ሥራው በዋናነት የክፍያ ሰነዶች በአዋጅ፣ በደንብና መመሪያ መሰረት ማዘጋጀት፣ የተሰብሳቢና ተከፋይ ሂሳቦች መረጃ ማጠናቀር የሚጠይቅ ሲሆን በአግባቡ ባይከናወን፣ የሚሰበሰቡና የሚከፈሉ ሂሳቦችን መረጃን ያዛባል ይህም ሪፖርት በወቅቱ እንዳይቀርብ በማድረግ የሥራ ክፍሉን ሥራ ያስተጓጉላል፡፡

 ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣

·         የለበትም፡፡

3.4 ፈጠራ

·         የሚሰበሰቡ መረጃዎችን ለአሰራር ምቹ አድርጎ ለማደራጀት በተለያ መረጃ ስርአት በመጠቀም ስራውን ያቀላጥፋል፡፡

3.5. የሥራግንኙነት /Work Communication/

3.5.1  የግንኙነት ደረጃ

·         ሥራው ከስራ ክፍሉ ሠራተኞች፣ ከኃላፊው፣ ከተቋሙ የተለያዩ የስራ ክፍሎች ጋር እንዲሁም ከተቋሙ ውጭ ካሉ የተለያዩ ተቋማትና ሌሎች አገልግሎት ፈላጊዎች ጋር ይገናኛል፡፡

3.5.2 የግንኙነቱ ዓላማ

·         ለክፍያ፣ ለሪፖርት፣ ለመረጃ ልውውጥ የሚያጋጥሙ ፋይናንስ ነክ ችግሮች ለማረም የሚያደርገው ግንኙነት ነው፣

3.5.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ

·         ከሥራ ጊዜው አስከ 40 በመቶ የሥራ የግንኙነት ማድረግ ይጠይቃል፡፡

3.6 ኃላፊነት

3.6.1 ኃላፊነት ለነዋይ

·         በዓመት አስከ 1 ሚሊየን ብር የሚገመት የክፍያ ሰነድ ያማዘጋጀት ኃላፊነት አለበት፡፡

3.6.2 ኃላፊነት ለሰው ሃብት

·         የለበትም፡፡

3.6.1.2 የኃላፊነት ዓይነትና ደረጃ

 

3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት

·         ሥራውን ለማከናወን የሚያግዙ ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ ኮምፒዩተር፣ ካልኩሌተር ግምታቸው እስከ 40 ሺህ ብር የሚገመት ንብረት በጥንቃቄ መያዝና በአግባቡ የመጠቀም ኃላፊነት አለበት፡፡

3.7. ጥረት

 3.7.1  የአዕምሮጥረት

·         ሥራው የክፍያ ሰነዶችን ማዘጋጀት፣ የተለያዩ ተከፋይና ተሰብሳቢ ሂሳቦችን ማጠናቀርን የሚጠይቅ ሲሆን መጠነኛ የሆነ የአእምሮ ድካም ያስከትላል ይህም ከስራ ሠዓት እስከ 30 በመቶ ይወስዳል፡፡

 3.7.2.ስነ-ልቦናዊ ጥረት

·         ሥራው ውጭ ተገልጋዮች ጋር ግንኙነት የሚጠይቅ በመሆኑ ስሜታዊነትን በመቋቋም፣ መመሪያና ደንቦችን አስረድቶ በትዕግሥት መሥራትን ይጠይቃል፣

3.7.3 የዕይታ ጥረት፣

·         የቀረቡ ሰነዶችን በሚገባ በማጣራትና በኮምፒዩተር መስራትና በማንበብ እንደዚሁም ሌሎች የመደመሪያ ማሽኖች ላይ በኮምፒዩተር መስራትና ማንበብ የዕይታ ጥረት የሚጠይቅ ሲሆን ይህም ከቀን የሥራ ጊዜው 30% ይሆናል፡፡

3.7.4 የአካልጥረት

·         ሥራው  ከ90% በመቶ በላይ በመቀመጥ የሚከናወን ነው፡፡

 

3.8. የሥራ ሁኔታ

3.8.1. ሥጋትና አደጋ

·         ሥራው ሥጋትና አደጋ የለበትም፡፡

3.8.2.  የሥራ አካባቢ ሁኔታ

·         ሥራው በምቹ የሥራ አካባቢ የሚከናወን ነው፡፡

 

ተፈላጊ የትምህርት ደረጃና የሥራ ልምድ

--በአካዉንቲንግ፣በአካዉንቲንግና ፋይናንስ የመጀመሪያ ዲግሪና 0ዓመት፣

ደረጃ VIII

ብዛት 1

Applicant Instruction | የአመልካቾች መመርያ

ማሳሰቢያ ፡-

- ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት ክፍት የስራ መደብ ለመወዳደር የምትፈልጉና መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች የተሟላ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃዎች ኦሪጅናልና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከ(cv) ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

-ከተጠቀሰዉ የትምህርት ደረጃ በላይ ያላቸዉ አመልካቾች መወዳደር ይችላሉ፣

- የመመዝገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይካሄዳል፡፡

-የመመዝገቢያ ቦታ ከሜክስኮ ወደ ቄራ በሚወስደዉ መንገድ ቡልጋሪያ ጫፍ በሚገኘዉ ያሬድ አረጋዊ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ የሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይሆናል፡፡

-በማስታወቂያዉ ላይ የተመለከተዉ በአዲሱ የነጥብ የስራ ምዘናና የደረጃ አወሳሰን ጥናት የደመወዝ  ስኬል አፈፃፀም መመሪያ መሠረት የሚከፈል ይሆናል፡፡

-ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡

-ለሾፌር I የስራ መደብ አመልካቾች ብቻ የስራ ልምድ ላላቸዉ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡

ለበለጠ መረጃ በድረ-ገጻችን፡-www.erpa.gov.etይመልከቱ

ስልክ ቁጥር፡-0114705585