Driver I (ሾፌር I)

  • ETHIOPIAN RADIATION PROTECTION AUTHORITY
  • Addis Ababa
  • Federal Government
  • Deadline Feb 27, 2020
Full time Logistics, Transport and Supply Chain

የስራው መደብ ዝርዝር

2.1. የሥራ መደቡ ዓላማ፡-  

·         እስከ 12 ሰው መቀመጫ ባላቸው ተሸከርካሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት የመስሪያ ቤቱ ሥራ ውጤታማ እንዲሆን መደገፍ ነው

3.1  የሥራ ውስብስብነት ፣

·         ሥራው እስከ 12 ሰው መቀመጫ ባላቸው ተሸከርካሪ ሽከርከር፣  እያንዳንዱን የተሽከርካሪ አካል በየጊዜው መፈተሸ፣ የቴክኒክ ችግሮችን እየተከታተሉ ደህንነቱን መጠበቅ፣ የትራፊክ ሕጎችን ሁልጊዜ ጠብቆ ማሽከርከር፣ የእያንዳንዱን ደንበኛ ፍላጎት ጠብቆ አገልግሎት መስጠትን የሚጠይቅ ሥራ ነው፤

·         ሥራው ሲከናወንም ያልተጠበቁ የተሸከርካሪ ቴክኒክ ችግሮች መፈጠር/ ፍሬን እና መሪ ከቁጥጥ ውጭ መሆን፣ ራዲያተር ድንገት ከሚጠበቀው በላይ መሞቅ፣ የትራፊክ ምልክቶች በለሌሉበት መልክዓም-ምድራዊ አቀማመጥና ሁኔታዎችን አመዛዝኖ መንዳት ፣ አስቸጋሪ/ ጉም፣ ዶፍ ዝናብና ጭጋግ አየር ሁኔታ አንዲሁም ጨለማ  በሚሆንበት ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ የሚከናውን ሲሆን

·         እነዚህንም ተሸከርካሪው በየወቅቱ ደህንነቱ ተፈትሾ ሠርቪስ እንዲደረግ በማድረግ፣ የትራፊክ ደህንነት መመሪያዎችን ጠንቅቆ በመረዳት፣ የአየር ሁኔታና ጨለማ በሚሆንበት ወቅት ለዕይታ እስከሚመች ድረስ ቆሞ በማሳለፍ፣ ፍጥነት በመቀነስ ሁልጊዜ ጥንቃቄ በተሞላ ሁኔታ በማሽከርከር ችግሮችን መፍታትን ይጠይቃል፡፡

3.2  ራስን ችሎ መስራት

3.2.1ሥራው የሚከናወንበት አግባብ

·         ሥራው የመንገድ ትራፊክ ሕጎች፣ ደንቦች እና የአነዳድ ጥንቃቄ መርህዎችን መሠረት በማድረግ የሚከናወን ነው፡፡

3.2.2 ሥራው የሚጠይቀው የክትትልና ድጋፍ ደረጃ

·         ሥራው በአግባቡ ስለመከናወኑ በቅርብ ኃላፊው አልፎ አልፎ ክትትልና ድጋፍ ይደረግበታል።

3.3 ተጠያቂነት

3.3.1 ተጠያቂነት  ለሥራ ውጤት /Responsibility for Impact/፣

·         ሥራው በአግባቡ ባይከናወን ወይም የሚፈጠሩ ስህተቶች በቶሎ ባይታረሙ በተሸከርካሪው ላይ የመጋጨትና የመገልበጥ በንብረትና በሕይወት ላይ አደጋ የማድረስ፤ እንደ አደጋውም ሁኔታ አሽከርካሪውንና የሥራ ክፍሉን ተጠያቂ ያደርጋል፣ የመሥሪያ ቤቱን ሥራ ያስተጓጉላል፣ የንብረትና የገንዘብ ኪሣራ በተቋሙ ላይ ያደርሳል፡፡

3.3.2 ተጠያቂነት ለሚስጥራዊ መረጃ፣

·         የለበትም፡፡

3.4 ፈጠራ

·         ሥራው በጉዞ ላይ ቀላል ብልሽቶች ሲያጋጥሙ ሞዴፊክ በመሥራት፣ የነዳጅ መሥመሮች ቢበጠሱ በመቀጣጠል፣ የመብራትና የባትሪ መሥመሮች ቢቆረጡ በማያያዝ የራሱን ፈጠራ ተጠቅሞ እስከተፈለገበት ጉዞ ድረስ ማድረስን የሚጠይቁ ፈጠራዎች ይኖሩታል።

3.5. የሥራ ግንኙነት /Work Communication/

3.5.1  የግንኙነት ደረጃ

·         ከውስጥ፡- ከሥራ ክፍሉ ኃላፊዎች፣ ከግዥና ፋይናንስ፣ ከንብረት አስተዳደር፣ ከመሥሪያ ቤቱ ሠራተኞች፣ ከጋራዥ፣ ነዳጅ አዳይ

·         ከውጭ፡- ከመንገድ ትራነስፖርት ደህንነት ተቆጣጣሪዎች፣ ከትራፊክ ተቆጣጣሪ ፖሊስ ግንኙነት ያደርጋል፡፡

3.5.2 የግንኙነቱ ዓላማ

·         የሥራ መመሪያ ለመቀበል፣ ሪፖርት ለማድረግ፣ አገልግሎት ለመስጠት፣የነዳጅ ሂሳብ ለማወራረድ፣   መረጃ ለመስጠት እና ለማስጠገን

·         ከውጭ፡- ስለ ሕጋዊነቱ መረጃ ለመስጠት ግንኙነት ያደርጋል፤

3.5.3 የግንኙነቱ ድግግሞሽ

·         የስራው የግንኙነት ድግግሞሽ ከስራ ጊዜው እስከ 25 በመቶ ይወስዳል፡፡

3.6 ኃላፊነት

3.6.1 ኃላፊነት ለሰው ሀብት

  3.6.1.1 በኃላፊነት የሚመራቸው ሠራተኞች ብዛት

·         የለበትም

 3.6.1.2 የኃላፊነት አይነትና ደረጃ

·         የለበትም

3.6.2  ኃላፊነት ለንዋይ

·         የለበትም

3.6.3 ኃላፊነት ለንብረት

·         ሥራው ተሽከርካሪ ከነሙሉ መፍቻ እና ክሪክ፣ ተቀያሪ ጎማ ጭምር እስከ 500,000 ብር ድረስ ዋጋ ያለው ንብረት ኃላፊነት አለበት

3.7. ጥረት   

 3.7.1  የአዕምሮ ጥረት

·         ሥራው የጎን ስፖኪየን እየተከታተሉ ርቀትን መጠበቅ፣ መልክዓምደራዊ አቀማመጥ አኳያ ፍጥነት ማመጣጠን፣ የትራፊክ ሕጎችን አስቦ ለመተግበር እስከ 20% የአእምሮ ጥረትን ይጠይቃል።

 3.7.2.ስነልቦናዊ ጥረት

·         ሥራው ከተገልጋዩ ሠራተኛ እና ከስራ ኃላፊዎች የሚደርስ ቁጣ፣ በጫካ፣ በማያውቀው አካባቢ እና በጨለማ ሲጓዝ በውስጡ የሚፈጠር ፍርሃትን ተቋቁሞ መሥራትን ይጠይቃል

 

3.7.3 የዕይታ ጥረት፣

·         ሥራው የትራፊክ ሕጎችን በጥንቃቄ ተከታትሎ ለማሽከርከር ሁልጊዜ ዕይታን ይጠይቃል ይህም ከሥራ ጊዜው 80 በመቶ ይወስዳል።

3.7.4 የአካል ጥረት በመቶ

·         ሥራው 30 በመቶ በመቀመጥ የሚከናወን ሲሆን ቀሪው 70 በመቶ የአካል ጥረት በሚጠይቅ ሥራ በመሥራት ጎንበስ ቀና በማለት፣ በመንቀሳቀስ፣ በመዘወር እና በመንጋለል የሚከናወን ነው።

3.8. የሥራ ሁኔታ

3.8.1. ሥጋትና አደጋ

·         ሥራው በስራው ክንውን ወቅት መኪናው የመጋጨት እና የመገልበጥ፣ በአካል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ብሎም እስከ ሞት የሚያደርስ ጉዳት እንዲሁም በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት ሊያስከትል ይችላል።

3.8.2.  የሥራ አካባቢ ሁኔታ

ሥራው በመኪና ጭስ፣ አቧራ፣ የተለያዩ የሚኪና አካላት ብናኞች የትንፋሽ፣ የቴታኖስ በሽታ፣ በመቀመጥ ብዛት በሚፈጠር ሙቀት የክንታሮትና የፊንጢጣ በሽታዎችን ሊያስከትሉ ይችላሉ።

Applicant Instruction | የአመልካቾች መመርያ

ማሳሰቢያ ፡-

- ከዚህ በላይ በተዘረዘሩት ክፍት የስራ መደብ ለመወዳደር የምትፈልጉና መስፈርቱን የምታሟሉ አመልካቾች የተሟላ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃዎች ኦሪጅናልና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ከ(cv) ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

-ከተጠቀሰዉ የትምህርት ደረጃ በላይ ያላቸዉ አመልካቾች መወዳደር ይችላሉ፣

- የመመዝገቢያ ጊዜ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ይካሄዳል፡፡

-የመመዝገቢያ ቦታ ከሜክስኮ ወደ ቄራ በሚወስደዉ መንገድ ቡልጋሪያ ጫፍ በሚገኘዉ ያሬድ አረጋዊ ህንፃ 2ኛ ፎቅ ላይ የሰው ኃብት ልማትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይሆናል፡፡

-በማስታወቂያዉ ላይ የተመለከተዉ በአዲሱ የነጥብ የስራ ምዘናና የደረጃ አወሳሰን ጥናት የደመወዝ  ስኬል አፈፃፀም መመሪያ መሠረት የሚከፈል ይሆናል፡፡

-ሴት አመልካቾች ይበረታታሉ፡፡

-ለሾፌር I የስራ መደብ አመልካቾች ብቻ የስራ ልምድ ላላቸዉ ቅድሚያ ይሰጣል፡፡

ለበለጠ መረጃ በድረ-ገጻችን፡-www.erpa.gov.etይመልከቱ

ስልክ ቁጥር፡-0114705585