የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ቀጥሎ በተጠቀሱት የሥራ መደቦች ሥራ ፈላጊ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል፤ለመወዳደር የሚፈልጉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች በተጠቀሰው ጊዜ እና ቦታ ማመልከት ይችላሉ፡፡
ተፈላጊ ችሎታ
- በአውቶ መካኒክ ወይም በአውቶሞቲቭ የቴክኒክና ሙያ ዲፕሎማ (10+3) እና በአውቶ መካኒክ ወይም በአውቶሞቲቭ ሥራ 6 ዓመት የሥራ ልምድ ያለው/ላት፣
ደረጃ
ብዛት
የሥራ ቦታ
- የምዝገባ ጊዜ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት፣
- የምዝገባው ቦታ በኢንስቲትዩቱ ዋና መ/ቤት እና በቁሉምሳ እና በአቦቦ ግብርና ምርምር ማዕከላት ሰው ሀብት አስተዳደር ቢሮ ሲሆን፣ ለቁሉምሳና አቦቦ ምርምር ማዕከላት ያመለከቱ ዕጩ ተወዳዳሪዎች የመምረጫ ፈተና የሚሰጠው በማዕከላቱ ነው፤
- ከሐምሌ 2011 ዓ.ም.ጀምሮ በሥራ ላይ በዋለው በአዲሱ በነጥብ የሥራ ምዘናና ደረጃ አወሳሰን የመንግስት ሠራተኞች የደመወዝ ስኬል መሰረት ነው፤
- አመልካቾች ማሟላት ያለባቸው የማመልከቻ ቅጽ መሙላት፣የተሟላ የትምህርት፣የሥራ ልምድና ሌሎች ማስረጃዎች ከማይመለስ ፎቶ ኮፒ ጋር ተያይዞ መቅረብ አለባቸው፤በቂ ስልክ ወይም አማራጭ አድራሻ በማመልከቻቸው ላይ መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡
- የዋናው መ/ቤት የምዝገባ ቦታ አድራሻ፡-ቦሌ ክፍለ ከተማ መገናኛ አካባቢ ወረዳ 6 በአምቼ ኩባንያ በኩል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ ወይም በኢትዮጵያ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ በኩል ወረድ ብሎ ነው፡፡
- ለመወዳደር የሚፈልጉ ዕጩ ተወዳዳሪዎች በተጠቀሱት ቦታዎች በግንባር በመቅረብ ወይም በወኪል ወይም
- በፖስታ ልከው መመዝገብ ይችላሉ፤
- ሴት ተወዳዳሪዎች እንዲያመለክቱ ይበረታታሉ፣
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116-45-44-41- ወይም 0116-46-01-74 ወይም (022-331-29-21 (ቁሉምሳ) መደወል ይቻላል፡፡ ፖ.ሣ.ቁ. 2003 (አዲስ አበባ)
የኢትዮጵያ የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት